ሜድቴክ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ መድኃኒት ፋብሪካ ጋር በመተባበር ሰሞኑን በመስቃን እና ማረቆ ወረዳዎች አዋሳኝ አካባቢ በተከሰተው ግጭት በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ አደጋ በመፈጠሩ ምክንያት ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች መልሶ ማቋቋም በሚደረገው ጥረት እንደሁልግዜውም ሰብአዊነትን በማስቀደም አጋር በመሆኑ ግምታቸው 200000 (ሁለት መቶ ሺህ) የሆኑ የተለያዩ ህይወት አድን መድኃኒቶችን እና በጥሬ ገንዘብ 200000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በድምሩ የ 400000 (አራት መቶ ሺህ) ብር እርዳታ ያደረገ ሲሆን በቀጣይነትም የተፈናቀሉት ዜጎቹን በዘላቂነት ወደ መደበኛ ኑሯቸው ተመልሰው ኑሯቸውን እስኪጀምሩ ድረስ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ የሜድቴክ ኢትዮጵያ መስራች እና  የኢትዮጵያ መድኃኒት ፋብሪካ ቦርድ ሊቀመንበር ዶ/ር መሐመድ ኑሪ ገልፀዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትና በሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አዋሳኝ በነበረው ግጭት ለተፈናቀሉ ዜጎች መልሶ ማቋቋሚያ በሚደረገው ጥረት አጋር በመሆን የኢትዮጵያ መድኃኒት ፋብሪካ ለወገኖቹ በ ገንዘብ የ2000000 (ሁለት ሚሊየን) ብር ድጋፍ እና ግምቱ 4000000 (አራት ሚሊዮን) ብር የሆኑ 52 መኖርያ ቤቶችን በማስገንባት መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ላይ ህዝባዊ ወገንተኝነቱን እንዳስመሰከረ ይታወሳል፡፡

 

 

Share